Covid 19 Information
ኮሮና ና የህዳር በሽታ ቻይና ዉሃን ግዛት ውስጥ ሰዎች እየሞቱ ነው በሽታው የዱር አራዊት ሥጋ በተመገቡ ሰዎች ነው የጀመረው እየተባለ በመገናኛ ብዙሃን መዘገብ ከተጀመረ ከድሴምበር (ታህሳስ) ወር መጀመሪያ ጀምሮ ቀናት ሳምንታትና ወራት አለፉ የአለርት ሆስፒታልም ይህን ዜና ሰምቶ ሁሉም የስሞኑ መወያያ አድርጎታል በአሜሪካ ፕሬዚደንቱን ጨምሮ የቻይና በሽታ እያሉ አሹፈዋል በዛን ሰሞን አሜሪካ ውስጥ እንደ ሲዲሲ ዘገባ በጉንፋን 1 መቶ ሰማኒያ ሺ ሰው ሆስፒታል ገብቶ ነበር 10ሺ ሞተዋል የበሽታ መቆጣጠሪያ ባለስልጣናቱ ይህ በየአመቱ የጉንፋን ወቅት ተለመደ ነው በማለት ችላ ብለው ነበር በጥቅምት ወር የጀመረው ይህ ኮቪድ አስራ ዘጠኝ( covid 19) የተባለ በሽታ ሁሉንም ታላላቅ አገራት አዳርሶ ህዝብ እየጨረስ በመጋቢት ወር መጀመሪያ…