የሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል አገልግሎት የታካሚዎች መብትና ግዴታ

የሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል አገልግሎት የታካሚዎች መብትና ግዴታ

የሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል አገልግሎት

የታካሚዎች መብትና ግዴታ

 1. 1የታካሚ መብቶች

1.1. በሆስፒታል የሚሰጠውን ሕክምና የማግኘት መብት

 • በሆስፒታል የሚሰጠውን የሕክምና አግልግሎት የማግኘት መብትዎ ካለበቂ ምክንያት በስተቀር የተጠበቀ ነው፣
 • አለርት ሆስፒታል በበቂ ሁኔታ አሟልቶ ሊሰጥ የዘረዘራቸውን የሕክምና አገልግሎቶች ተገልጋዩ የማግኘት መብት አለው፣
 • ማንኛውም ተገልጋይ በፆታዊ ክፍፍል፣ በሀይማኖት ወይም በእምነት፣ጾታዊ ትንኮሳ፣ በአካል ጉዳት (ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው) ፣በዕድሜ ከአድሎ ነፃ የሆነ አገልግሎት የማግኘት መብት አልዎት፣

1.2. የአካባቢ ደህንነትና እና ጥራቱን የተጠበቀ ሕክምና የማግኘት መብት

 • ደረጃውን የጠበቀ ሕክምና በበቂ ክህሎትና ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች አገልግሎት የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ነው፣
 • ሆስፒታሉን የመመልከት፣እንዲሻሻል፣የመፈፀም አቅም ያላቸው የጤና ባለሙያዎች እንዲሟሉ አስተያየት የመስጠት መብት አለዎት፣

1.3. የመከበር፤ፍቃድዎን የመጠየቅና ሚስጥርዎን የመጠበቅ መብት

 • ሰብአዊ ክብርዎ በተጠበቀ መልኩ ሕክምና የማግኘት መብት አለዎት፣
 • የሚሰጠዎትን ሕክምና የመቀበልም ሆነ ያለመቀበል መብት ያሎት ሲሆን፤ በአካልዎ ላይ ለሚደረጉ ማንኛውም ምርመራዎች በቂ ግንዛቤ አገኝተው ሲስማሙ ብቻ የሚፈፀም ይሆናል፡፡ ይህንን ግንዛቤ ለመውሰድ ያሉበት ሁኔታ የማይፈቅድ ከሆነ ሌላ በእርስዎ በኩል በህጋዊ መንገድ ፍቃድ ባገኘ ሰው የሚወሰን ይሆናል ወይም በእርሶ በጎ ፍቃድ የሚወሰን ይሆናል፡፡
 • የሚሰጠውን ሕክምና አስቀድሞ ለታካሚው በማሳወቅ ሊያስከትል ስለሚችለው ጥቅምና ጉዳት በግልፅ የማወቅ መብት አልዎት፣
 • በሆስፒታሉ ሲታከሙ ደህንነትዎና ሚስጥርዎ በተጠበቀ ሁኔታ ህክምና የማግኘት መብትዎ የተረጋገጠ ይሆናል፣
 • የህክምና ግላዊ መረጃዎን የማግኘት መብት ያሎት ሲሆን ይህ መረጃ በሚቀጥሉት ጊዜያት በፍቃድዎ ለሚያደርጉት ምርመራ ግብአት ሆኖ የሚያገለግል ይሆናል

1.4. ስለህክምናዎ በሆስፒታሉ ያለዎት ተሳትፎና በዕቅድና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ፣

 • ማንኛውም ተገልጋይ ህብረተሰብ ሆስፒታሉ በሚያደርገው የአገልግሎት ማሻሻያ ውይይት ላይ የመሳተፍና ሃሳብ የመስጠት መብት አለው
 • በሆስፒታሉ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የመሳሰተፍና ይጠቅማሉ የሚሏቸውን መረጃዎችን በጽሁፍ በማቅረብ ሆስፒታሉ ለሚያዘጋጀው እቅድ ግብአት የመስጠት መብት አልዎት

1.5. ቅሬታን የማቅረብና ምላሽ ስለማግኘት

 • በሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ካለዎት የማቅረብና ቅሬታዎ በትክክል የመታየት መብትዎ የተጠበቀ ይሆናል፣
 • ያቀረቡት ቅሬታ ተጣርቶ ውጤቱን የማወቅ መብትዎ የተጠበቀ ነው፣
 • ባቀረቡት በማንኛውም ቅሬታ ላይ በቂ ምላሽን ካላገኙ ወደ ሆስፒታሉ የበላይ ኃላፊ ቅሬታዎትን ማቅረብ ይችላሉ፣
 • በችልተኝነት በተፈፀመብዎት ጉደት ላይ ተመጣጣኝ የሆነ ካሣ በህግ አግባብ የማግኘት መብትዎ የተጠበቀ ነው፣
 1. 2የተገልጋዮችና የማህበረሰቡ ሀላፊነት
 • የእርስዎንና የቤተሰብዎን ጤና ለመጠበቅ የእርስዎ ሃላፊነት አስተዋፆኦና መኖር አስፈላጊ ነው፣
 • የማዕከሉንም ሠራተኞች ሆነ ወደ ሆስፒታሉ የመጡ ሌሎች ታካሚዎችን የማክበር ግዴታ ሲኖርቦት፣በማንኛውም መንገድ እርስዎ ለሚፈጥሩዋቸው አላስፈላጊ ድርጊቶች በህጉ መሰረት የሚጠየቁ ይሆናሉ፣
 • ስለራስዎ ጤንነት ሁኔታ ትክክለኛ መረጃ የመስጠት ሀላፊነት ይኖርቦታል፣
 • የሕክምና ቀጠርዎን ጠብቀው ሊታከሙና ሕክምናዎት የሚጠናቀቀው ባለሙያ ውሳኔ ይሆናል፣
 • ሕክምናዎትን በትክክል በመውሰድ፤አስቸጋሪ ሁኔታ ከገጠምዎ ሐኪምዎትን ሊያማክሩ ይገባል፣
 • ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ በአስፈላጊ የጤና ፕሮግራሞች ላይ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል ለምሳሌ፡- እንደ ክትባት
 • በማንኛውም ባገኙት አውንታዊና አሉታዊ የህክምና አገልግሎት እንዲሁም የጎንዮሽ ጠንቅን አካቶ ለሚፈጠርብዎ የጤና ችግር አፋጣኝ ግብረ-መልስና አስተያየት እንዲሰጡ እንጠይቃለን!!

Leave a Reply